ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ (1884 -1963ዓ/ም) ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ከአባታቸው ከመሪጌታ ወልደ ጻድቅ ሰሎሞን፤ ከእናታቸው ከወይዘሮ ወለተ ማርያም ባዩ (በኋላ እማሆይ ወለተ ማርያም) በሰሜን ሸዋ ዞን መርሐ ቤቴ አውራጃ ሚዳ ሚካኤል በተባለ ቦታ መጋቢት14 ቀን1884 ዓ.ም ተወለዱ:: በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት በዓርባ ቀናቸው በአጥቢያቸው ኮሶ ማርያም በተባለች ቤተ ክርስቲያን ተጠምቀው ገብረ ጊዮርጊስ ተብለው ስመ ክርስትና ተሠየሙ:: እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በዚያው በትውልድ ቀዬአቸው በአመልሳ ኮሶ ማርያም ግብረ ዲቁና ተምረው ከግብፃዊው የኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳሳት አቡነ ማቴዎስ መዓርገ ዲቁና ተቀብለው ቤተ ክርስቲያን ሲያገለግሉ ቆዩ:: በመቀጠልም ወደታላቁ ገዳም ደብረ ሊባኖስ በመሄድ ጸዋትወ ዜማ፣ የቅኔና የመጻሕፍት ትርጓሜ ትምህርታቸውን ከመምህር ገብረ ኢየሱስ፣ የቅዳሴውን ትምህርት ከአባ ገብረ ሕይወት ተምረው አጠናቀቁ፡፡ ቅዱስነታቸው በዚህ ዓይነት ትምህርታቸውን በማስፋፋት፣ በዚያው በደብረ ሊባኖስ ገዳም ውስጥም በረድዕነት እያገለገሉ ሥርዓተ ገዳምን ሲማሩ ከቆዩ በኋላ ነሐሴ 24 ቀን 1905 ዓ.ም በ21 ዓመታቸው ሥርዓተ ምንኩስና ተፈጸመላቸው:: በ1906 ዓ.ም ከግብፃዊው የኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳሳት አቡነ ማቴዎስ መዓርገ ቅስና ተቀበሉ። በ1909 ዓ.ም በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ትዕዛዝ በመናገሻ ግርጌ ለሚሠራው የቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለሚጠጉ መነኮሳትና ባሕታውያን የሚሠሩትን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያኑን አስተዳደር ረዳት እንዲሆኑ በተጠየቁት መሠረት መነኮሳቱን እያስተማሩ ለሦስት ዓመታት በመናገሻ ቅድስት ማርያም ገዳም ቆዩ። በዚህ አንቅስቃሴ ላይ እያሉም ንግሥት ዘውዲቱ ያሠሯት የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን በመጠናቀቋ በ1916 ዓ.ም የገዳሟ መምህር (አበ ምኔት) ሆነው ተሾሙ፡፡ በየካቲት 27 ቀን 1924 ዓ.ም የመናገሻ ቅድስት ማርያም ገዳምን መምህርነት እንደ ያዙ የአዲስ አበባ መንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ደብር አለቅነት በግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተሾሙ፡፡ ሁለቱንም ቅዱሳት መካናት በትጋት እያስተዳደሩ ሳሉ በ1926 ዓ.ም በቅድስት ሀገር ኢየሩላሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ራይስ ሆነው ተሾሙ:: ከሁለት ዓመት አገልግሎት በኋላ ከኢየሩሳሌም ወደኢትዮጵያ በመምጣት በግርማዊነታቸው መልካም ፈቃድ የካቲት 24 ቀን 1927 ዓ/ም «ብፁዕ ዕጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ ዘነበረ በመንበረ ተክለ ሃይማኖት»ተብለው የታላቁ የደብረ ሊባኖስ ገዳም 59ኛ እጨጌ ሆነው ተሾሙ።
ሙሉውን ጽሑፍ አንብብ
ይህ ኮርስ መሰረታዊ ጽንሰ-ሀሳቦችን እና የትምህርት ዓይነቶችን አጠቃላይ እይታ ይሰጣል በሥነ-መለኮት ውስጥ. ተማሪዎች የስነ-መለኮታዊ አስተሳሰብን ታሪካዊ እድገት ይቃኛሉ፣ ቁልፍ ሥነ-መለኮታዊ ቃላት፣ እና ዋናዎቹ የነገረ-መለኮት ቅርንጫፎች፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ፣ ስልታዊ፣ ታሪካዊ እና ተግባራዊ ሥነ-መለኮት.
ይህ ኮርስ በመካከላቸው ያለውን ግንኙነት ለመረዳት የተቀናጀ አካሄድ ያቀርባል ቱሪዝም እና የቅርስ አስተዳደር. ተማሪዎች እንዴት ባህላዊ፣ ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ቅርሶችን ይቃኛሉ። በቱሪዝም ልማት ላይ ተጽእኖ ያሳድራል እና በተቃራኒው. ኮርሱ የሚያሻሽሉ ዘላቂ ልምዶችን ያጎላል የቅርስ ቦታዎችን ታማኝነት በመጠበቅ የጎብኝዎች ልምድ።
ይህ ኮርስ የህግ እና የህግ መሰረታዊ መርሆችን እንደ መግቢያ ሆኖ ያገለግላል ስርዓት. ተማሪዎች የህግን ምንነት፣ የህግ ምንጮች እና የህግን ሚና በህብረተሰብ ውስጥ ይመረምራሉ። የኮርሱ ሕገ መንግሥታዊ፣ የወንጀል፣ የፍትሐ ብሔር እና የአስተዳደርን ጨምሮ የተለያዩ የሕግ ዘርፎችን ይሸፍናል።
No published articles available.
No scheduled events found.
ስለ ኮሌጁ ስኬቶች፣ ስለ ስነ-መለኮት ሲምፖዚየሞች እና ስለ መጪ የአካዳሚክ ምዝገባ ማብቂያ ቀናት መረጃ ያግኙ።